Labels

Showing posts with label የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት. Show all posts
Showing posts with label የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት. Show all posts

Monday, May 30, 2016

መልእክት ፡ ኀበ ፡ ሰብአ ፡ ኤፌሶን፡፡ (2)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!



የሐዋርያው ፡ የጳውሎስ ፡ መልእክት ፡ ወደ ፡ ኤፌሶን ፡ ሰዎች፡፡

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

‹‹ወአርአየነ ምክረ ፈቃዱ በከመ ሥምረቱ›› (ኤፌ. 1፡9)!

v  የጥናቱ መግቢያ

·  የኤፌሶን ቤተ፡ ክርስቲያን የተመሰረተችው በሐዋርያው ጳውሎስ ሁለተኛ ሐዋርያዊ የአገልግሎት ጉዞ ነው፡፡

·  ሐዋርያው በቆሮንቶስ ከተማ ለ18 ወራት ከነበረው የአገልግሎት ቆይታ በኋላ (ሐዋ. 18፡11)፤ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመሆን ኤፌሶንን ጎብኝቷል (ሐዋ. 18፡18)፡፡

·  ሐዋርያው በኤፌሶን የነበረው የመጀመሪያ ቆይታ ለአጭር ጊዜ የነበረ ሲሆን፤ ዳሩ ግን እንደሚመለስ ቃል ገብቶላቸው ነበር (ሐዋ. 18፡19-21)፡፡ ነገር አዋቂ፤ በመጻሕፍት እውቀት የበረታ፤ የጌታን መንገድ የተማረ፤ የዮሐንስን ጥምቀት የሚያውቅ፤ በመንፈስ የሚቃጠል፤ ስለ ኢየሱስ የሚናገርና በትክክል የሚያስተምር ለሆነው አጵሎስ ‹‹የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት›› የተባለላቸው ጵርስቅላና አቂላ በኤፌሶን ቆይተዋል (ሐዋ. 18፡24-26)፡፡

· ሐዋርያው በሦስተኛ ሐዋርያዊ ጉዞው ወደ ኤፌሶን የተመለሰ ሲሆን፤ በዚያም ለሦስት ዓመታት በአገልግሎት ቆይቶአል (ሐዋ. 19፡8-10፤ 20፡31)፡፡ አንደኛ እና ሁለተኛ የቆሮንቶስ መልእክታትን የጻፈው በእስያ ዋና ከተማ ከሆነችው ከኤፌሶን ነው (1 ቆሮ. 16፡8፤9)፡፡ በዚያ ብዙ ድንቅና ተአምራት በእርሱ በኩል ተከናውነዋል (ሐዋ. 19፡12)፡፡

· ሐዋርያው በእድሜው ማብቂያ ከኤፌሶን አስጠርቶአቸው ከመጡ ሽማግሌዎች (ባለ አደራ) ጋር በሚሊጢን እንደተገናኘ፤ ምክርና ማስጠንቀቂያ አዘል የስንብት መልእክት አስተላልፏል (ሐዋ. 20፡16-38)፡፡

Friday, April 29, 2016

መልእክት ፡ ኀበ ፡ ሰብአ ፡ ኤፌሶን፡፡ (1)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


የሐዋርያው ፡ የጳውሎስ ፡ መልእክት ፡ ወደ ፡ ኤፌሶን ፡ ሰዎች፡፡

አርብ ሚያዚያ 21 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

    ‹‹ወአርአየነ ምክረ ፈቃዱ በከመ ሥምረቱ›› (ኤፌ. 1፡9)!

·        የመልእክቱ ጸሐፊ፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜ፡ ከ61-63 ዓ/ም ባሉት ዓመታት
·        መልእክቱ የተጻፈበት ቦታ፡ ሮም
በጊዜው የመልእክቱ ተቀባዮች፡ የኤፌሶን ቤተ፡ ክርስቲያን (ማኅበረ ምእመናን)
·        የመልእክቱ ጭብጥ፡ የክርስቶስ ባለ ጠግነት በቤተ፡ ክርስቲያን 
(The Orthodox study Bible) 

Saturday, April 9, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡ (8)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 


ቅዳሜ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)!››

No. 14-17, ‹‹While the master-slave relationship continues, it is transcended by brotherhood in Christ.›› /The Orthodox Study Bible; New Testament and Psalms New King James Version/.

‹‹አምኀከ ኤጳፍራስ ዘተጼወወ ምስሌየ በኢየሱስ ክርስቶስ፡፡››
‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ . . ››፡-

          ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ መልእክት የስንብት ክፍል የጠቀሰው ሌላው የተወደደ አገልጋይ ኤጳፍራ ነው፡፡ ሐዋርያው ይህንን መልእክት የጻፈው በእስር ቤት ሆኖ እንደ መሆኑ፤ አብሮት ስለ ክርስቶስ የታሠረ ሌላውን አገልጋይ ይጠቅሳል፡፡ ባለፈው ጥናታችን ሐዋርያው ከእስር ተፈትቶ በፊልሞና ቤት ያለችውን ቤተ ክርስቲያን እንደሚጎበኛት ያለውን ተስፋ ለተወደደውና አብሮት ለሚሠራ ለፊልሞና ሲገልጽለት አይተናል፡፡

        በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለ ኤጳፍራ የምናገኘውን ምስክርነት በመመልከት የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያስተምረንን እንወስዳለን፡፡ በቆላስይስ መልእክት ‹‹ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ ተማራችሁ፤ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፡፡ ደግሞም በመንፈስ ስለሚሆን ስለ ፍቅራችሁ አስታወቀን፡፡›› (ቆላ. 1፡7-8) የሚል ምስክርነት በሐዋርያው ተጽፎ እናነባለን፡፡   

Friday, April 8, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(7)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


አርብ መጋቢት 30 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)!››

‹‹አእሚርየ ከመ ትወስክ እንዘ አዘዝኩከ፤ ካዘዝሁህም አብልጠህ እንድትሠራ ዐውቄ ጻፍኩልህ፡፡›› /ቁ. 21/

         ፍቅርን ለሚመለከቱ ቅን ልቦች የፊልሞና መልእክት መዋደድን ሊሞላን የሚችል ቅዱስ አሳብ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ግንኙነቶቻችንን የምንጠብቅበት ሰማያዊ መመሪያና መለኮታዊ አካሄድን በጥልቀት እንረዳበታለን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልሞና እና በአናሲሞስ መካከል የተፈጠረውን መለያየት አስመልክቶ ‹‹ልቡን  የሚያሳርፍ›› መፍትሔ እንዲመጣ በፍቅር ዝቅ ማለቱን እንመለከታለን፡፡ በአገራችን የሰዎችን አለመግባባት ለመፍታት የሚያስተራርቁ ሰዎች ድንጋይ ጭምር ተሸክመው በመካከል እንደሚቆሙ እናውቃለን፡፡

        በዚህ አጭር መልእክት ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሥር ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ኢዮብ ‹‹ይኸው ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፤ ስታሻክሩኝም አላፈራችሁም›› (ኢዮ. 19፡3) እንዳለ፤ እንዲሁም በልማድ ‹‹አሥር ጊዜ አትነዝንዘኝ›› እንደሚባል (ይህንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያለው የመጽሐፉ ኢዮብ ይመስለኛል)፤ ሐዋርያው ለቆሮንቆስ ምእመናን ‹‹ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (1 ቆሮ. 1፡10) ያለውን እዚህም ተግባራዊ እንዳደረገ ልናስብ እንችላለን፡፡     

Monday, March 14, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(6)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


 ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት


(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)!››

‹‹ወእመሰ እኁየ አንተ ተወከፎ ከማየ፤ ለእኔስ ወንድሜ ከኾንህ እኔ እንደ ተቀበልሁት ተቀበለው፡፡ አንድም ለእኔ ወንድሜ ከኾነ እኔን እንደ ተቀበልህ ተቀበለው››፡፡

‹‹ . . እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው ›› /ቁ. 17/

        ሐዋርያው ጳውሎስ አናሲሞስን ‹‹እንደ እኔ›› ተቀበለው በማለት ይጠይቀዋል፡፡ ፊልሞና ጳውሎስን ተቀብሎ ለዘላለም እንደያዘው እናውቃለን፡፡ አሁንም በወንጌል እውነት በማመን ወደ ክርስትና የተቀላቀለውን አናሲሞስን ፊልሞና ጳውሎስን በተቀበለበት በዚያው መቀበል ሊቀበለው የተገባ ነው፡፡ ‹‹እንደ ባልንጀራ ብትቆጥረኝ›› ሲል በሁለቱ መካከል ያለውን የቀረበ ወዳጅነት ማስተዋል እንችላለን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹ባልንጀራህን እንደ ራስህ›› (ማቴ. 19፡19) የሚለውን ቅዱስ ትእዛዝ እንዴት ተግባራዊ እንዳደረገ በዚህ አጻጻፉ ልብ እንላለን፡፡

        አስቀድመን ባየናቸው ቁጥሮች ውስጥ ‹‹ስለ ልጄ›› ‹‹ልቤ እንደሚሆን›› በማለት ፊልሞና አናሲሞስን ይቀበለው ዘንድ ለምኖአል፡፡ እውነተኛ ልጅ ደግሞ አባቱን መምሰሉ እውነታ ነው፤ እንደ እኔ ተቀበለው ማለቱም የአናሲሞስን እውነተኛ መለወጥ፤ የጳውሎስንም እውነተኛ መውደድ እናይበታለን፡፡ እንዲህና እንደዚያ ነው ልንል በማንችልበት ሁኔታ በጳውሎስና በፊልሞና መካከል ልዩ የሆነ መቀራረብና ጥብቅ ወዳጅነት እንደ ነበር ከመልእክቱ መረዳት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው ክርስትና መልክ ክርስቶስን ማሳየቱ ዛሬ ላለነው ወቀሳም ጭምር ነው፡፡

Tuesday, March 1, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(5)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ማክሰኞ የካቲት 22 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)!››

v ‹‹ሳልማከርህ ምንም እንኳ ላደርግ አልወደድሁም ›› /ቁ. 14/

          ባለፈው ጥናት ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹ሐዋርያዊ ሥልጣኑን›› መሰረት ባደረገ መንገድ ሳይሆን፤ 
1. እድሜውን (እኔ ሽማግሌው)፤ 
2. የኢየሱስ ክርስቶስ እስር መሆኑን፤ 
3. የፊልሞና ሕሊና በጎነት፤        
4. በመካከላቸው ያለውን የእምነትና ፍቅር አንድነት ማእከል በማድረግ 
          የሁሉም ነገር ማሠሪያ በሆነው ‹‹ስለ ፍቅር›› ለምኖታል፡፡ (ዮሐንስ አፈወርቅ)         

        አናሲሞስን በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ እርሱ ጋር በመሆን እንዲያገለግለው ሊያስቀረው ፈቅዶ ነበር፡፡ ዳሩ ግን አሳዳሪው ከነበረው አሁን ደግሞ በክርስቶስ ወንድሙ ከሆነው ከፊልሞና ጋር መመካከርን እንደ ወደደ ይገልጻል፡፡ በዚህ መልእክት ውስጥ ከምናየው የክርስቶስን ፍቅር ማዕከል ያደረገ እውነተኛ ግንኙነት አንጻር፤ በኋላ ፊልሞና አናሲሞስን ያገለግለው ዘንድ ወደ ሐዋርያው ጳውሎስ መልሶ ሊልከው እንደሚችል ልናስብ እንችላለን፡፡ ዳሩ ግን ሐዋርያው ምንም ሥልጣን ያለው ቢሆንም እንኳ የፊልሞና በጎነት በፈቃዱ እንጂ በማስገደድ እንዳይሆን ተጠንቅቋል፡፡

Tuesday, February 16, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(4)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)!››

‹‹ሐዋርያው ጳውሎስ በተገኘበት ቦታ ሁሉ በጥልቅ ትህትና የተመላለሰ፤ ባሮችን ነጻ የሚያወጣውን እና ከጌቶቻቸው ጋር የሚያስተካክላቸውን፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጆች የሚያደርገውን የወንጌል ኃይል የገለጠ ነው›› /ከቀደሙት፡ - ቲዎዶሬት/

‹‹የእምነት ኅብረት›› /ቁ. 6/

          ከሞት በኋላ የሚቀጥል አብሮነት ከእምነታችን ኅብረት የሚመጣ ነው (1 ዮሐ. 1፡3)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው›› (ሮሜ 10፡17) እንዲል፤ እውነተኛ እምነት በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ላይ የቆመ ነው፡፡ ፊልሞናን በተመለከተ ‹‹የእምነትህም ኅብረት›› ተብሎአል፡፡

         በቀደመው ጥናታችን በፊልሞና ቤት ውስጥ ክርስቲያኖች በኅብረት ይሰባሰቡ እንደነበር አይተናል፡፡ ይህም ኅብረት ‹‹ሁለት ወይም ሦስት በስሜ›› (ማቴ. 18፡20) የሚለውን እውነት ማእከል ያደረገ ነው፡፡ ‹‹ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ›› በተባለለት በፊልሞና አገልግሎትም የክርስቲያኖቹ (ቅዱሳን) ልብ አርፎአል፡፡

Tuesday, January 26, 2016

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(3)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)››!

·  ጸሐፊው፡- ሐዋርያው ጳውሎስ ሲሆን፤ መልእክታቱን በአገልግሎት አጠገቡ ሆነው በሚረዱት እርሱ እየተናገረ ያጽፍ እንደ ነበር (ሮሜ 16፡22፤ 1 ቆሮ. 16፡21፤ ገላ. 6፡11፤ ቆላ. 4፡18፤ 2 ተሰ. 3፡17)፤ ነገር ግን ለፊልሞና የተላከውን ይህንን መልእክት በገዛ እጁ እንደ ጻፈው ይነግረናል (ፊል. 19)፡፡
·  የተጻፈበት ጊዜ፡- የፊልሞና መልእክት የቆላስይስ መልእክት በተጻፈና በተላከ ጊዜ በተመሳሳይ ከሮም (ሐዋርያው በእስር ቤት ሳለ) አብሮ የተላከ መልእክት ሲሆን፤ ጊዜውም ከ61 – 63 ዓ/ም ባለው ወቅት እንደ ሆነ ይታሰባል፡፡
· የመልእክቱ ጭብጥ ፡- ሁላችንም ባሮች የነበርን ሲሆን፤ ነገር ግን በክርስቶስ ወንድሞችና እህቶች ነን የሚል ነው፡፡

     ‹‹የተወደደ፤ የሚለው አገላለጽ ሙገሣን አልያም ልዩ መሆንን የሚያሳይ ሳይሆን፤ ጥልቅ የሆነ ፍቅርን ለማሳየት የተነገረ ነው፡፡ . . . አብሮን ለሚሠራ፤ የሚለው ደግሞ ወንጌልን ከማስፋትና ሌሎችን ወደ እምነት ከማምጣት ጋር በተያያዘ ያለውን አገልግሎት በተመለከተ የተነገረ ነው፡፡›› /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

       ሌሎችን መውደድ በሌለበት፤ በትክክል እግዚአብሔርን ማመን አይኖርም፡፡ በክርስትና ውስጥ አብሮ መሥራት ከመዋደድ ባነሰ ነገር ላይ ሊመሠረት አይችልም፡፡ ጌታ ለጴጥሮስ ትልቅ ኃላፊነት ሲሰጠው፤ አስቀድሞ የጠየቀው ‹‹ትወደኛለህን?›› (ዮሐ. 21፡15-17) በማለት ነበር፡፡ ፊልሞና በሌሎች ወንድሞች ልብ ውስጥ የተወደደ መሆኑ ጌታን ከመውደዱ የተነሣ እንደ ሆነ ልንረዳ እንችላለን፡፡

Friday, December 25, 2015

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(2)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


አርብ ታኅሣሥ 15 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 3፡1)››!

           መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ከመክፈታችሁ፤ እንዲሁም የመልእክቱን ክፍል ከመግለጣችሁ አስቀድሞ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ፤ አንድ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማስተዋልን እንዲሰጣችሁ፤ እንዲሁም ከመልእክቱ ልትረዱ የሚገባችሁን ሁሉ መቀበል እንድትችሉ በቅዱስ መንፈሱ በኩል እንዲረዳችሁ በመንፈስና በእውነት በመገዛት ጸልዩ፡፡ ተወዳጆች ሆይ፤ ከዚህ በኋላ መልእክቱን ቃል በቃል በጥንቃቄና በእርጋታ አንብቡት፤ ይህንንም በመደጋገም አድርጉት፡፡

የመልእክቱ ዳሰሳ፡-

o   ‹‹ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው . . ›› /ቁ. 15/ የመልእክቱ ዋና አሳብ ሲሆን፤ ለመልእክቱ ‹‹የዘላለም መያያዝ›› ብለን ርእስ ልንሰጠው እንችላለን፡፡ ሐዋርያው ለፊልሞና ‹‹እንደ ባልንጀራ ብትቆጥረኝ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው›› /ቁ. 17/ በማለት ይጠይቃል፡፡

o   መልእክቱ ከሐዋርያው ከጳውሎስ መልእክታት በጣም አጭሩ መልእክት ሲሆን፤ ሐዋርያው በእስር ቤት ሆኖ ከጻፋቸው ከፊልጵስዩስ፤ ከቆላስይስ እና ከኤፌሶን መልእክታት መካከል አንዱ ሲሆን፤ ይዘቱ ግን የተለየ ነው፡፡


o   ሐዋርያው ከጻፋቸው መልእክታት መካከል ለሦስት ሰዎች (ግለሰቦች) የጻፋቸው አራት መልእክታት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህም፡- አንደኛ ጢሞቴዎስ፤ ሁለተኛ ጢሞቴዎስ፤ ቲቶ እና አሁን እያጠናነው ያለነው የፊልሞና መልእክት ናቸው፡፡ መልእክቱን ወደራሳችሁ አቅርባችሁ፤ ለእናንተ እንደተላከ በመቁጠር ብታነቡት በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡

o   በመልእክቱ አሳብ ውስጥ ቁልፍ የሆኑ (ትኩረት የሚሰጣቸው) ቃላትን እናገኛለን፡፡ እነዚህም፡- ክብር፤ ቸርነት፤ ጥንቃቄ፤ ወዳጅ፤ ፍቅር፤ ትህትና፤ ጥበብ፤ ግልጽ የሆነ ንጽህና (ቅድስና)፤ ከዚህ በመነሣት የመልእክቱን ይዘት ‹‹ትህትናን የተላበሰ መልእክት›› እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ ተወዳጆች ሆይ፤ በዚህ መልእክት ውስጥ ችግር ፈቺ የሆነውን ክርስትና ለመመልከት ሞክሩ፡፡

o   መልእክቱ ባለ ሀብት የነበረው የቆላስይስ ክርስቲያን እና የሐዋርያው የጳውሎስ ቅርብ ወዳጅ የፊልሞና ባሪያ አናሲሞስ (ጠቃሚ፤ ዋጋ ያለው ማለት ነው) ከጌታው ወደ ሮም ኮብልሎ መጥፋቱ፤ በኋላም በክርስቶስ ክርስቲያን ሆኖ ወደ አሳዳሪው መመለሱን ማእከል ያደረገ ‹‹የእርቅ›› ደብዳቤ ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ፤ ጥሩ የማይባለውን አጋጣሚ ጌታ አንድን ነፍስ ወደ ክብር ለማምጣት እንዴት ለበጎ እንደ ተጠቀመበት አስተውሉ፡፡

o   መልእክቱ የ‹‹እርስ በርስ መዋደድን›› /ዮሐ. 13፡34/ አዲስ ትእዛዝ መሰረት ያደረገው የክርስትና ኑሮ የፍቅር ገጽታ ምን እንደሚመስል በተግባር የሚያስረዳ ሲሆን፤ በዓለም ላይ የሰዎች ባርነት (ስቃይን ጭምር የተሞላ) ተስፋፍቶ በነበረበት የሐዋርያት ዘመን ባሪያን አስመልክቶ የተጻፈ ብቸኛው መልእክት ነው፡፡ በዚህም ክርስትና የባርነትን ችግር ለመፍታት ያለውን የላቀ መንገድ የሚያሳይ ጽሑፍ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

o   ሐዋርያው በቆላስይስ መልእክቱ ላይ ‹‹ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ . . ›› /ቆላ. 4፡9/ ብሎ እንደጻፈው፤ ፊልሞና በቆላስይስ የሚኖር ባሪያ አሳዳሪና ቤተክርስቲያኒቱም (የምእመናን ስብስብ) በቤቱ የነበረች እንደሆነ፤ እንዲሁም የፊልሞና መልእክት እና የቆላስይስ መልእክት በተመሳሳይ ጊዜ የተጻፉና የተላኩ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በዚህ ክፍል መሰረት መልእክቱ የተላከው ‹‹በአናሲሞስና በቲኪቆስ›› እጅ ነው፡፡    

Thursday, December 17, 2015

መልእክት ኀበ ፊልሞና፡፡(1)


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ሐሙስ ታህሳስ 7 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

(መልእክት ወደ ፊልሞና)

‹‹እምጳውሎስ ሙቁሐ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ (ኤፌ. 31)››!

          የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ እድገት መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ በስብከትና በንባብ የምናዘወትረውን የእግዚአብሔር ቃል በጥናት መልክ ለመረዳት መሞከር፤ ጊዜ መድቦ መመርመር ከክፍሉ የበለጠ እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡ በክርስትና ኑሮአችን ቋሚ የሆነ፤ አማራጭ የማናስቀምጥበት ‹‹ቃሉን የማጥናት ጊዜ›› ቢኖረን እራሳችንን፤ እንዲሁም በዙሪያችን ያሉትን እንጠቅማለን፡፡

         ተወዳጆች ሆይ፤ ያለ እግዚአብሔር ቃል በማንሻገረው የአሁኑ ዓለም ቋሚ ውጊያ እንዲሁም  በዲያብሎስ ሽንገላ መካከል እንደምንመላለስ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ . . . የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው›› /ኤፌ. 6፡17/ ይለናል፡፡ በሚታየው ዓለም የማይታየውን መንፈሳዊ ውጊያ በመንፈስ ሰይፍ ካልሆነ በቀር ድል ልናገኝ አንችልም፡፡

Monday, February 23, 2015

መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት የሚሆን ምክር፡


ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2007 የምሕረት ዓመት
1.    መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ አጥና፡፡ 
መጽሐፍ ቅዱስን ሳያስታጉሉ ማጥናት ትልቅ በረከት ነው።
/ እንጀራ የሥጋ ምግብ እንደሆነ የእግዚአብሔር ቃልም የመንፈስ ምግብ ነውና። «ሰው በእንጀራ ብቻ ሊኖር አይቻልም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ።›› (ማቴዎስ፡44)፤ ‹‹ለሚጠፋ መብል አትድከሙ፤ ለዘለዓለም ለሚኖረው ምግብ (መብል) እንጂ›› (ዮሐ.627)፡፡
/ ማጥናትን አንድ ቀን የተውህ እንደሆነ ፈጽሞ ለመተው ልምድ ምናልባት ይሆንብሃልና።
/ ምግብ ለሰውነት አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ለመንፈሳዊ ሕይወት አስፈላጊ ነው። ሙዋቹ የእንግሊዝ ንጉሥ ጆርጅ 5 ማናቸውም ሥራ ቢኖርባቸው መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ያነቡ ነበር ይባላል። ጆን ክሪዞስቶም በሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት በየቀኑ ከሚያጠኑት በላይ የሮሜን መልእክት በሳምንት ሁለት ጊዜ ያነቡት ነበር። በየቀኑ 20 ምዕራፍ የሚያነብ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ በየቀኑ ብዙ ምዕራፍ ማጥናት አስፈላጊ አይደለም። ነገር ግን ጥዋት አንድ ምዕራፍ ወይም የምዕራፍ አንድ ክፍል ቢቻልም ማታ ሌላ ምዕራፍ ማጥናት አስፈላጊ ነው።