Wednesday, April 10, 2013

ሰቆቃወ ፍቅር



እሮብ ሚያዝያ 2/2005 የምሕረት ዓመት

    የሠላሳ ሁለት ዓመት እድሜ ያላት ሲሴሊያ ከባለቤቷ አዳም ጋር በፍቅር ያሳለፈችውን ጊዜ በቀላሉ ልትረሳው፣ በሰዎች የማጽናኛ ቃል ልታልፈው፣ እንደ አሮጌ ኑሮ ቆጥራው አዲስ ምዕራፍ ልትጀምር አቅም አልነበራትም፡፡ የሞተው ባለቤትዋ ስርዓተ ቀብሩ እንዳበቃ ከመቃብር አውጥታ በአልጋዋ ላይ በማስተኛት ለሁለት ዓመታት ያህል ቀን አብራው በመዋል፣ ሌሊቱን አብራው በማደር አሳልፋለች፡፡ የባሏ እስትንፋስ የተቋረጠ ቢሆንም እርሷ ለእርሱ የነበራት ፍቅር ሕያውነት ግን ቀጥሏል፡፡

    ስለ እርሱ ስትናገርም “አዳምን ምን ጊዜም ቢሆን አልረሳውም፡፡ በአካል ቢሞትም ልቤ ላይ ግን ሕያው ነው፡፡ እርሱ በጣም አስደናቂ ሰው ነበር፡፡ አጽሙን ከእኔ ጋር በማኖሬ ተጽናንቻለሁ፡፡ ፍቅሬንም ተወጥቻለሁ፡፡” በማለት ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን የባለቤቷን አጽም ወደ መቃብሩ በመመለስ ሄንሪ የተባለ ሰው አግብታለች (ትንግርት መጽሔት፣ ግንቦት/ሰኔ 1985፣ ገጽ 5)፡፡

    አንዳንድ ሰዎች ፍቅር ልክ እንደ እቅፍ አበባ ለሌላው የሚሰጥ ነገር እንደ ሆነ ሲያስቡ ሌሎች ደግሞ በላይህ ላይ የተጣለ የማይረባ ግን ደግሞ የጠነከረ ኃይል ነው በማለት ይስማማሉ፡፡ ፍቅር ግን ልንሰጠው የምንችለው ማንኛውም ነገር አይደለም፡፡ ፍቅር ራሱ ሌሎች ነገሮችን እንድንሰጥ የሚያስችለን ከፍተኛ ግፊት ነው፡፡ ጥንካሬን፣ ኃይልን፣ ነፃነትንና ሰላምን ለሌሎች እንድንሰጥ የሚረዳን ጉልበት ፍቅር ነው፡፡

    ከዚህ አሳብ በመነሣት ፍቅር ውጤት ሳይሆን መንስዔ፣ ወራጅ ሳይሆን ምንጭ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከፍቅር የተነሣ የማንሰጥ ከሆነ፣ ከፍቅር የተነሣ ይቅር የማንል ከሆነ፣ ከፍቅር የተነሣ የማንራራ ከሆነ፣ ከፍቅር የተነሣ ለእውነት የማንኖር ከሆነ በእኛ ያለው የፍቅር ኃይል ተዳክሟል አልያም ሞቷል ማለት ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ እጅግ የከበረውና ቀዳሚው ነገር ሌላውን ማፍቀር ነው፡፡ በማስከተልም በሕይወት ውስጥ እጅግ የከበረው ነገር በሌላው መፈቀር ነው፡፡ በመጨረሻ እጅግ የከበረው ነገር ከላይ የተመለከትናቸው ሁለቱ በእኩል ጊዜ መሆን ሲችሉ ማለትም ባፈቀሩት ሰው ሲፈቀሩ ነው፡፡

      የሰው ፍቅር ልዩ ልዩ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፍቅር አንድ መሆኑ ዘመን የማይሽረው መጽናኛችን ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን እንዴት እንደወደደን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “እንዲሁም ዓለም አንተ እንደላከኝ በወደድከኝም መጠን እነርሱን እንደወደድካቸው ያውቃሉ” (ዮሐ. 17÷23) ይላል፡፡ እግዚአብሔር እኛን የወደደን ፃድቅ፣ የዋህና ትሁት የሆነውን እስከ መስቀል ሞትም የታዘዘውን አንድ ልጁን በወደደበት ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር ሲወድ የሰውን ማንነት ታሳቢ አድርጎ አይደለም የምንለው፡፡ መልክና ቁመና፣ ሀብትና ሥነ ምግባርን ግምት ውስጥ በማስገባት አልያም ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ሰውን መውደድ የሰው ፍቅር እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡

      ፍቅር የሰውን ልማድ ይሻገራል፡፡ ጥሙን ሳያረካ፣ ርሀቡን ሳያጠግብ፣ መሻቱን ሳይሞላ አይዝልም፡፡ ከንቱ በሆነው በዚህ ዓለም መለፍለፍ ውስጥ ያለው የማይሰለች አጓጊ ወሬ ፍቅር ነው፡፡ ደመ ነፍስ በሆኑ እንስሳት ውስጥ እንኳ ይህ ኃይል መታየቱና መሥራቱ ምንኛ ድንቅ ነው! አብዛኛውን ጊዜ መልካም በምንላቸው ነገሮች ውስጥ ምቾትን ብቻ እናስተውላለን፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ተከትሎ መራብ መቸገር፤ ማዘን መከፋት የለበትም የሚለው ሙግት ምንጩ ይኸው አመለካከት ነው፡፡ በዓለም ሳለን መከራ እንዳለብን ግን እናውቃለን (ዮሐ. 16÷33)፡፡ አፍቅረን ካፈቀርነው ጋር፣ ደክመን ከደከምንለት ነገር ጋር፣ ዋጋ ከፍለን ከለፋንለት ነገር ጋር ላንኖር ወይም የእኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰው ባይነጥቀን እንኳ ሞት ተናጥቆን ይሆናል፡፡ ምድር በብዙ ፍትሐዊ ባልሆኑ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከዚህም የተነሣ ዓለም በብዙ ሙሾና ለቅሶ፤ ሰቆቃና እንግልት እረስርሳለች፡፡ 

Tuesday, March 26, 2013

ትልቁ ጉድለት



ማክሰኞ መጋቢት 17/2005 የምሕረት ዓመት

“. . . በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ፡፡ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል፡፡” (ኤፌ. 2÷12)

        ምድራችን ሰዎች ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የሚራወጡባት አደባባይ ናት፡፡ ከትንሽ እስከ ትልቅ ሁሉ ለፍላጎቱ ከእንባ ጀምሮ እስከ ሞት ድረስ ዋጋ ሲከፍልም እንመለከታለን፡፡  በተገኘው አጋጣሚና በቻለው መጠን ሁሉም ሀዘኑን በደስታ፣ ሁከቱን በሰላም፣ ማጣቱን በማግኘት፣ ውርደቱንም በክብር ለመለወጥ ጥረት ያደርጋል፡፡ አቅም እምቢ ቢል እንኳ አሳብ ይፍጨረጨራል፡፡ ሰው ሁሌና ሁሉ እንደማይሞላ መረዳቱ አያሳርፈውም፡፡ እንዲያውም ከፊት ይልቅ ጥማቱ እየጨመረ ይመጣል፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓለም የሚኖረንንን ሩጫ መጨረሻው ምን እንደሆነ ስንፈትሸው ከሥጋ ስኬት የዘለለ ሆኖ አናገኘውም፡፡  ብዙ ሰው ከደህና ቤተሰብ አለመወለዱ፣ አድጎ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ራሱን አለማግኘቱ፣ ከባልንጀሮቹ እኩል በሥጋ ነገር አለመለወጡ፣ በዚህ ዓለም ነገሮች የተደላደለ ነገር በሕይወቱ ብዙ ጉድለት መኖሩ የብቻ አሳብ አጀንዳው፤ የሰው ፊት የወሬ ርዕሱ ነው፡፡

        የእግዚአብሔር ቃል  ስለ ሰው ልጆች ትልቅ ጉዳት ሲናገር ግን “ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ” ይላል፡፡ ሐዋርያው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ክርስቲያን ለሆኑ የኤፌሶን ምእመናን “ነበራችሁ” በማለት የሆነላቸው ነገር ከነበሩበት ኑሮ ምን ያህል የላቀና እንደ አዲስ መፈጠር እንደ ሆነ ያስረዳል፡፡ ሰው ተስፋን ካጣ የመኖር ትልቅ ኃይሉን አጣ ማለት ነው፡፡ ሀብትና ቁሳቁስ፣ ሥልጣንና ክብር ኖሮን ተስፋችን ከሞተ ግን ሕይወት ትቀጥ ዘንድ በቂ አቅም ታጣለች፡፡ ተስፋ ሁለነገራችን የተያያዘበት ሰንሰለት ነው፡፡ ሰው ተስፋው ከተቆረጠ ሕይወት እንድትቀጥል ዕድል የለውም፡፡ በባሰ ነገር ላይ ተቀምጠን የተሻለ የምንጠብቀው ተስፋ ስለምናደርግ ነው፡፡ የሰውን ኃጢአተኝነት ተከትሎ የመጣው ቀላል የማይባል ውድቀት እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍርድ ነው፡፡ በሰው ሕይወት ውስጥ የዔደን ገነትን ለቅቆ ከመውጣት ጋር በተያያዘ ብርቱ ተስፋ ነበር፡፡ ያም መዳናችን ነው! ብዙዎች ሳያዩ የተስፋውን ቃል በማመን ከዚህ ምድር አልፈዋል፡፡ እኛ ግን እንዲህ ያለውን መዳን ከዚህ ምድር ጀምሮ እንድናጣጥም ጌታ ረድቶናል፡፡

Wednesday, March 13, 2013

ከዚህም ጹም



ከቁጣና ከጥላቻ ጹም ለባልንጀሮችህ የበዛ ፍቅርን ስጥ፡፡
ከመለያየት ጹም ቢቻልህስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑር፡፡
በሌሎች ላይ ከመፍረድ ጹም ማንንም ሰው ከመዳኘትህ በፊት እግዚአብሔር ጥፋቶቻችንንእንዴት እንደሚመለከት አስተውል፡፡  
ለራስ ከሚሰጥ አነስተኛ ግምት፣ ከጨለምተኝነትና አሉታዊ ከሆነ አስተሳሰብ ጹም ስለሕይወት በሚኖርህ አመለካከት ሁሉ ሚዛናዊ ሁን፡፡  
ተስፋ ከመቁረጥ ጹም ይህ የቁም ሞት ነውና በምታደርገው ነገር ሁሉ ተስፋ ይኑርህ፡፡
ከማጉረምረም ከፍርሃትና ከጭንቀት ጹም ጌታ ለሙሉ ሕይወታችን ያስባልና እምነትህንበእርሱ ላይ ጣል፡፡
ከስንፍና ጹም በሚያስፈልግህ ሁሉ በጸሎትና በምልጃ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቅ፡፡
ሕይወትን ካከበዱብህ ችግሮች፣ ወድቆም ከመቅረት ጹም የደስታዎችህን ጊዜያት ሁሉልትደሰትባቸዉ ጣር፡፡
ከምሬት ጹም የደስታዎችህን ጊዜያት ሁሉ ልትደሰትባቸው ጣር፡፡
አብዝቶ ለራስ ከመጨነቅ ጹም ራስህን ምን ጊዜም በጌታ እግር ሥር አድርግ፡፡
ከማንኛውም ዓይነት ቅሬታ አልያም ቂም ጹም የበደሉህን ሁሉ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታይቅር በል፡፡ 
ከአሉባልታና ፌዝ ከተቀላቀለበት ወሬ ጹም እውነተኛ በሆኑና በደስታ ለዛ በተሞሉ ቁምነገሮች ውስጥ ተሳተፍ፡፡
ከአባካኝነትና ከአጥፊነት ጹም መውጣትና መግባትህ በመጠን ይሁን፡፡ 
ለዓለም አብዝቶ ከመጨነቅ ጹም ተጨማሪ ጊዜ ለአምላክህ ለመስጠት ትጋ፡፡ 
ከክፉ ልማዶችህ ጹም አንተ የተፈጠርከው በእግዚአብሔር አምሳል ነው፡፡

    ልብ በሉ! ዛሬ ምድራችን የምትጨነቀው ከመብል ተከልክለው ነገር ግን ከእነዚህየክፋት አውራዎች መፆም ባልቻሉ ወገኖች ነው፡፡ ለሚበልጠው ያትጋን!

Tuesday, March 5, 2013

አሜን እንደ አቀበት




ማክሰኞ የካቲት 26/2005 የምሕረት ዓመት

         የሰዓቱ መገስገስ፣ የሰማዩ  መዳመን፣ የንፋሱ ሽውታ፣ የጀንበርዋ ማዘቅዘቅ፣ ልክ እንደ ገደል ማሚቱ ኑሮዬን ያሳበቀብኝ ያህል ተሰማኝ፡፡ ከጥያቄ ወደበለጠ ጥያቄ፣ ከእንባ ወደ ባሰ እንባ፣ ከፈተና ወደ ብርቱ ፈተና መገላበጤን ልቤ ልክ እንደ ሰው እየታዘበው ለዚህ የተፈጠርኩ ያህል ቆጥሬው የአሳብም የእግርም ጉዞዬን በምሬት ኃይል እገፋለሁ፡፡ ትላንትና ዛሬ፤ ቅድምና አሁን ተጨፍልቀው አንድ ሆነውብኛል፡፡

     ሁሉም ነገር ለምሬት ምክንያት የሆነ ያህል ተሰማኝ፡፡ ከሰው ዘንድ ምክርም ልግስናም ጨርሻለሁ፡፡ የባሰ ነግረው ሊያጽናኑኝ፣ ስለተጎዳ አውርተው ሊጠግኑኝ፣ ከኑሮ ተሞክሮአቸው መክረው ሊመልሱኝ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል፡፡ ይህ ግን ችግሬን ለማረሳሳት እንደ ማዳፈኛ ያህል ብቻ ነበር እንጂ ዘላቂ እረፍት አልሰጠኝም፡፡ ከሰው ቃል የእግዚአብሔር ቃል፣ ከሥጋ ለባሽ ማጽናናት የመንፈስ ቅዱስ ማጽናናት፣ ከምድራዊ መፍትሔ የመለኮት ምላሽ እንዲሻል ልቤ ግድ ስላለኝ አሳቡ ከሚሰበክበት፣ ምስጋናው ከሚደርስበት፣ ኃጢአተኛ በምሕረት ከሚመለስበት አደባባይ ለድምፁ ቅርብ፣ ለታዳሚው ሩቅ ሆኜ ጥግ ላይ ቁጭ አልኩ፡፡ የመከራዬ እድሜ እንደተደገፍኩት የጥድ ዛፍ ያህል መሰለኝ፡፡ በዕለቱ የነበረው ሰባኪ “እግዚአብሔር አለ” ሲል ቃሉ ጆሮዬ ጋር ደረሰ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ባለ ድምፅ “አሜን!” አሉ፡፡
        
       ባለፉት ልምምዶቼ አሜንታ እንደ እኔ የሚቀለው፣ አፉንም ሞልቶ የሚናገረው አልነበረም፡፡ አሁን ግን እሩቅ እንዳለ የማስበውን እግዚአብሔር ቀርቶ የራሴን ሕልውና እንኳን እጠራጠራለሁ፡፡ እነርሱ እንደ መለሱት ልመልስ፣ እንደተስማሙት ልስማማ ውስጤ ታገለኝ፡፡ እናም ተሸነፍኩ፡፡
         

Tuesday, February 12, 2013

ሁሉ አይከፋም


                                ማክሰኞ የካቲት 5/ 2005 የምሕረት ዓመት

          በአንድ ምሽት በአላባማ አደባባይ አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት ሴት በብርቱ ከሚዘንበው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ራሷን ለማስጠለል እየጣረች ሊፍት የሚሰጣት ሰው በመፈለግ ቆማለች፡፡ ጉልበቶቿ እየተብረከረኩ፣ ንፋስ እያንገዳገዳት፣ በድንግዝግዝ አጥርታ ለማየት እየሞከረች የሚያልፈውን ሁሉ መኪና እጇን ዘርግታ እርዳታ ትጠይቃለች፡፡ ብዙዎች ለተማጽኖዋ ምላሽ ሳይሰጡ ሄዱ፡፡ አንዳንዶቹም ከለሯን እያዩ “ይበልሽ” አይነት ገላምጠዋትና የመንገዱን ዳር ውሃ እየረጩባት አለፉ፡፡ በመኪናዋ ብልሽት ምክንያት እንዲህ ላለ ጉስቁልና መዳረጓና እንደ እርሷ ሰው የሆኑ ሰዎች ሊረዱዋት አለመቻላቸው አበሳጫት፡፡ ድንገት ግን ጭብጥ ብላ በቆመችበት አንድ ነጭ ወጣት በ1960ዎቹ የነበረውን ግጭትና በመካከላቸው የተፈጠረውን ልዩነት እንደማያውቅ ሆኖ መኪናውን ፊት ለፊትዋ አቆመ፡፡ ከሞቀው ውስጠኛ ክፍል ወደ ቀዝቃዛው ወርዶ ሁኔታዋ የሚጠይቀውን ያህል እረዳት፡፡
          በተረበሸና በተጣደፈ ስሜት ውስጥ ብትሆንም ከልብ አመስግናው አድራሻውን ተቀብላ ተለያዩ፡፡ ታዲያ ከሳምንት በኋላ የዚህ ሰው ቤት ተንኳኳ፡፡ በሩን ሲከፍት በስጦታ መጠቅለያ የተሸፈነ ውድ ዕቃ ደጃፉ ላይ ተመለከተ፡፡ ከጎኑ ደግሞ ልዩ ማስታወሻ የሚል ፖስታ ተቀምጦአል፡፡ በውስጡም ያለው መልእክት እንዲህ ይላል፡- “በዚያች ምሽት፣ በዚያ አውራ ጎዳና፣ እንደዚያ ባለ ሁኔታ  ውስጥ አንድ ትልቅ ትምህርት በልቤ ላይ አስቀምጠሃል፡- “ሁሉ እንደማይከፋ ተረዳሁ” የአንተ መድረስ እኔን ከጨለማና ከብርድ መታደግ ብቻ ሳይሆን ባለቤቴ በሞትና በሕይወት መካከል ሳለ ከአልጋው አጠገብ ሆኜ እንድረዳው አድርጎኛል፡፡ ከሁሉ በላይ “ሰው ሁሉ ክፉ” እንዳልሆነ ተረድቼብሃለሁና ብሩክ ሁን”!

Tuesday, February 5, 2013

የቆቅ ትዳር (ክፍል ሁለት)


                                                             

                                  ማክሰኞ ጥር 28/2005 የምሕረት ዓመት

      በመጀመሪያው ክፍል ንባባችን በጋብቻው ቀን ትታው ዕጩ ባሏን በሰው ሁሉ ፊት እንደማታገባው ነግራው ስለሄደች ሴት አውርተን ነበር፡፡ ወደ ዛሬው አሳብ ከመሸጋገራችን በፊት ያለፈውን ጥያቄ እንመልስላችሁ፡፡ ሴቲቱ ጥላው እንድትሄድ ምክንያት የሆናት ነገር ምን መሰላችሁ? በእጮኝነት አብረው ባሳለፉባቸው ጊዜያት ሁሉ መደበኛ ፊርማው ምን ይመስል እንደነበር ስለምታውቅ የጋብቻቸው ቀን የፈረመው ፊርማ ትልቅና ደማቅ በመሆኑ ይህም ከሁል ጊዜው የተለየ አዲስ በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ለብዙዎቻችን ስሜት አይሰጥ ይሆናል፡፡ ዳሩ ግን ለዚህች ሴት ትልቅ መልእክት ነበረው፡፡ የመጀመሪያው “በዚህ ሰው ውስጥ የማላውቀው አዲስ ጠባይ አለ ማለት ነው” የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ “በትዳር ውስጥ ሊያሳየኝ ያለውን አምባገነናዊ አባወራነት የሚጠቁም ነው” የሚል ይሰኛል፡፡ በዚህ ሰው እውነተኛ ጠባይ ላይ የተደረገ በቂ ጥናት ይኑር አይኑር ባናውቅም በዚህች ሴት ስነ ልቦና መሠረት ግን የእጮኛዋ ጊዜ ጠብቆ ፊርማ መለወጥ ትልቅ መልእክት አስተላልፎላታል፡፡   

     የብዙ ባለ ትዳሮች አንዱ ሙግት “አዲስ ጠባይ” ነው፡፡ ካገባሁት በኋላ አዲስ ሆነብኝ፣ የማልላመደው ጠባይ ገጠመኝ የሚል ሮሮ፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ሰዎች ናቸው ከጋብቻ በፊት በሚኖረው አብሮነት (በተአቅቦ) እንደሚገባ የሚተያዩት? በሰውየው ከሚሸሸገው ጠባይ በላይ በእኛ አለማስተዋል ምክንያት በቸልታ የሚታለፍ የተገለጠ ጠባዩ ይበልጣል፡፡ በሕብረት ውስጥ ሁሉንም ማጥራት ባይቻልም ቢያንስ ችግሮቹን በአግባቡ ለይቶ ማወቅ ባያሳርፍ እንኳ ያዘጋጃል፡፡ ነገር ግን ስሜታችንን ብቻ እያዳመጥን ቸል የማይባሉ ነገሮችን (ትንንሾቹን ጨምሮ) ብንዘነጋቸው ዋጋ መክፈላችን አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ በታች የሳይኮሎጂ ባለ ሙያ የሆነ አንድ ወንድም የላከልንን እናስነብባችኋለን፡፡
 


   Commitment                              intimacy


                                         Passion

“ፍቅር በሳይኮሎጂ እይታ

         ስለ ፍቅር መጽሐፍ ቅዱስ፣ የተለያዩ ባለ ሙያዎች እንዲሁም ግለሰቦች ብዙ ብለዋል፤ እኛም ብዙ ሰምተናል ብዙ ብልናል፡፡ ለዛሬ ግን የሳይኮሎጂ ባለ ሙያዎች ስለ ፍቅር የሰጡትን ሙያዊ ትንታኔ ከራሳችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸርን እንመለከታለን፡፡ ከብዙዎቹ የስነ ልቦና ባለ ሙያዎች መካከል ግልጽ በሆነና በማያሻማ ሁኔታ ስለ ፍቅር ትንታኔ የሰጠ ባለ ሙያ ስተርንበርግ ይባላል፡፡ ይህ ባለ ሙያ እንደሚነግረን አንድ ሰው እየተሰማው ያለው ስሜት ፍቅር ይሁን አልያ ተራ ስሜት ማወቅ የሚቻለው እነዚህ ሦስት የፍቅር መሰረታዊያን መኖር ሲችሉ ነው፡፡ እነዚህ የፍቅር መሰረታዊያን ምን ምን ናቸው? በማለት ስንዘረዝራቸው፡ -

Friday, January 18, 2013

ከዚህም በላይ ደስታ!



                                     
                       

                                        ቅዳሜ ጥር 11/2005 የምሕረት ዓመት


       ከእያንዳንዱ ሰው ጥረት ጀርባ ያለው ጥልቅ መሻት ደስታ እንደሆነ ሁሉ በእግዚአብሔር አሳብ ውስጥ ያለው ከፍታም ደስታ ነው፡፡ እርሱ በሰው ታሪክ ውስጥ ያዘጋጀው ትልቁ ነገር ደስታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንንም ለሀዘን፣ ለሮሮረ፣ ለመከራና ስቃይ አልፈጠረም፡፡ ዛሬ የምናልፍበት የተበላሸ ነገር ሁሉ የሰው መበላሸት ውጤት ነው፡፡ ነገር ግን ሰው በየዘመናቱ በራሱ መንገድ ደስታን ሲያስስ ኖሮአል፡፡ የደስታ መገኛ ሀብት እንደሆነ ያሰቡ ሰዎች ለዚህ እስከ መጋደል ኖረዋል፣ የሰላም ምንጩ እውቀት እንደሆነ ያሰቡ ወገኖችም የቻሉትን ያህል ለመጠበብ ሞክረዋል፣ ደስታ የሚገኘው ሥልጣን በመያዝ እንደሆነ የተሰማቸው ሰዎችም ለዚህ ታምነው ኖረው አልፈዋል፡፡ ሁሉም በየተሰማራበት ተግባር ለመደሰት ዘወትር ይሻል፡፡

       ደስታን ስለ መፈለግ ስናስብ የጠቢቡ ሰሎሞንን ፍለጋ እናስታውሳለን፡፡ ብዙ ሰው ዝና ቢኖረው የማይቸገር፣ ሀብት ቢኖረው የማይርበው፣ ሥልጣን ቢኖረው የማያዝን ይመስለዋል፡፡ ከእነዚህ አንዱ እንኳ ቢኖረን እንባዎች ሁሉ ከአይኖቻችን እንደሚታበሱ እናስባለን፡፡ ዳሩ ግን ጠቢቡ ሰሎሞን እነዚህን ሁሉ ነገሮች በአንድነት ጠቅልሎ የያዘ ንጉሥ ነበር፡፡

       ኢትዮጵያዊቷ ንግሥተ ሳባ ዝናና ጥበቡን ሰምታ፣ ብዙ ጓዝና እጅ መንሻ ይዛ፣ ቀይ ባህርን አቋርጣ ነፍስ እስከማይቀርላት ድረስ የልቧን ሁሉ የገለጠችለት የእስራኤል ገዥ ነበር(1ነገ. 10÷1-10)፡፡ ለክብሩ የማይንበረከክና በጥበቡ የማይደመም ያልነበረለት ሰሎሞን የሕይወት ትርጉም የጠፋበት የደስታ አድራሻ ግር ያለው ሰው ነበር፡፡ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ሁለትን በመንፈስ ሆነን ስናጠና ጥበበኛው እንዴት ባለ ድካምና ጥረት ውስጥ እንዳለፈ የፍለጋውንም ከንቱነት እናስተውላለን፡፡