በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ቅዳሜ ሚያዝያ 3 ቀን 2007 የምሕረት ዓመት
‹‹ . . እትቤዝወከ በመስቀልየ ወበሞትየ››
‹‹ . . በመስቀሌና በሞቴ አድንሃለሁ።››
(ኪዳነ አዳም ፫፡፫-፮፤ ዘፍ.፫።፲፭)
‹‹ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ስመ መንግሥታቸው ከመስቀል ጋር የተጣመረ
ነበር፣ የቅዱስ ንጉሥ ላሊበላ (፩ሺህ፩፻፶፮ - ፩ሺህ፩፻፺፯ ዓ.ም) ስመ መንግሥቱ ገብረ መስቀል ሲሆን የእቴጌይቱ ስመ መንግሥት
መስቀል ክብራ ነበር፤ የዐፄ ይስሐቅም (፩ሺህ ፬፻፲፬ - ሺህ፩፬፻፳፱ ዓ.ም) ስመ መንግሥታቸው ገብረ መስቀል ነበር። የደብዳቤያቸውም
ርእስ ትእምርተ መስቀልና ኢየሱስ የሚል ነበር።
ኢ የ
+
ሱ ስ ›› /መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ ዮሐንስ/
በኢትዮጵያ ታሪክ የክርስትና እምነት ከቤተ መንግሥት ወደ ሕዝቡ እየወረደ
እንደተስፋፋ ይነገራል፡፡ ለዚህም ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ዋና ማሳያ የሚጠቀሰው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ነው /ሐዋ. 8፡26-39/፡፡
በአገራችን ወንጌል እንዲሰበክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲገለጥ፤ ክርስቶስ ትውልዱን እንዲገዛው ሕዝባችን ሰፊ እድል እንደነበረውና እንዳለው
አመላካች ታሪኮችን ከመዛግብት ልንረዳ እንችላለን፡፡ ዳሩ ግን ለእውነት የማይታዘዝ ኑሮ፤ የእግዚአብሔርን አሳብ የሚቃወም አመጽ፤
ከቃሉ በተቃራኒ የሆኑ ሥርዓቶች ሕዝቡን ያሰከሩ ጉሽ ወይን ጠጆች ሆነው በየዘመናቱ ዘልቀዋል፡፡



