በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት
‹‹ወአርአየነ
ምክረ ፈቃዱ በከመ ሥምረቱ›› (ኤፌ. 1፡9)!
v የጥናቱ መግቢያ
· የኤፌሶን ቤተ፡ ክርስቲያን የተመሰረተችው በሐዋርያው ጳውሎስ ሁለተኛ ሐዋርያዊ የአገልግሎት ጉዞ ነው፡፡
· ሐዋርያው በቆሮንቶስ ከተማ ለ18 ወራት ከነበረው የአገልግሎት ቆይታ በኋላ (ሐዋ. 18፡11)፤ ከጵርስቅላና ከአቂላ
ጋር በመሆን ኤፌሶንን ጎብኝቷል (ሐዋ. 18፡18)፡፡
· ሐዋርያው በኤፌሶን የነበረው የመጀመሪያ ቆይታ ለአጭር ጊዜ የነበረ ሲሆን፤ ዳሩ ግን እንደሚመለስ ቃል ገብቶላቸው ነበር
(ሐዋ. 18፡19-21)፡፡ ነገር አዋቂ፤ በመጻሕፍት እውቀት የበረታ፤ የጌታን መንገድ የተማረ፤ የዮሐንስን ጥምቀት የሚያውቅ፤ በመንፈስ
የሚቃጠል፤ ስለ ኢየሱስ የሚናገርና በትክክል የሚያስተምር ለሆነው አጵሎስ ‹‹የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት››
የተባለላቸው ጵርስቅላና አቂላ በኤፌሶን ቆይተዋል (ሐዋ. 18፡24-26)፡፡
· ሐዋርያው በሦስተኛ ሐዋርያዊ ጉዞው ወደ ኤፌሶን የተመለሰ ሲሆን፤ በዚያም ለሦስት ዓመታት በአገልግሎት ቆይቶአል (ሐዋ.
19፡8-10፤ 20፡31)፡፡ አንደኛ እና ሁለተኛ የቆሮንቶስ መልእክታትን የጻፈው በእስያ ዋና ከተማ ከሆነችው ከኤፌሶን ነው
(1 ቆሮ. 16፡8፤9)፡፡ በዚያ ብዙ ድንቅና ተአምራት በእርሱ በኩል ተከናውነዋል (ሐዋ. 19፡12)፡፡
· ሐዋርያው በእድሜው ማብቂያ ከኤፌሶን አስጠርቶአቸው ከመጡ ሽማግሌዎች (ባለ አደራ) ጋር በሚሊጢን እንደተገናኘ፤ ምክርና
ማስጠንቀቂያ አዘል የስንብት መልእክት አስተላልፏል (ሐዋ. 20፡16-38)፡፡