Thursday, September 19, 2013

የስንኝ ገበታ 1




            አርብ መስከረም 10/ 2006 የምሕረት ዓመት

ለእኔ ሲነጋ ለጠላት ጨልሟል፣
ጉልበቱ ቄጤማ ኃይሉም ከንቱ ሆኗል፡፡
ደኅንነት ዋስትና የያዘኝ መዳፍህ፣
ጌታ ነህ ኢየሱስ ማንም የማይደፍርህ፡፡


ከሰው የጨረሰ ልቡን ለሚያስታምም፣
ተስፋው ተጨልጦ ለመኖር ያጣ አቅም፡፡
 ትንሣኤና ሕይወት መንገድና እውነት፣
ክርስቶስ ኢየሱስ ፍቱን ነው መድኃኒት፡፡


ብዙ ተምሮ ትንሽ ከመስራት፣
ትንሽ ተረድቶ ብዙ ከማውራት፡፡
 ያድነኝ ጥበብህ ካንተ የቀጸልኩት፡፡


ከዚያ ፍቅር ከዚያ ደስታ፣
ለዘላለም እንዳልወጣ፣
ራራልኝ እዘንልኝ፣
ለኔ ብለህ የሞትክልኝ፡፡ አሜን!

No comments:

Post a Comment