በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
‹‹ኢከሰተ አፉሁ በሕማሙ›› እንዲል (ሐዋ. 8፡32)::
አርብ ሚያዚያ
21 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁለተኛው ክፍል ‹‹የታሪክ ክፍል›› በመባል
ይታወቃል፡፡ ይህም ከአገልጋዮቹ አንጻር ‹‹የሐዋርያት ሥራ››፤ ከሥራው ባለቤት አንጻር ደግሞ ‹‹የመንፈስ ቅዱስ ሥራ›› በመባል
የሚታወቀው መጽሐፍ ነው፡፡ ‹‹ለድፍርስ መፍትሔው ምንጭ መውረድ ነው›› የማወቅ መመሪያዬ ነው፡፡ የክርስትናን መሠረተ ጅማሬ ለሥጋና
ደም አሳብ ክፍተት በማይሰጥ መልኩ ቁልጭ ብሎ በምንመለከትበት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፤ በሞተውና ከሙታንም በተነሣው በክርስቶስ ክርስቲያን
የሆኑቱ በኅብረት የተቀበሉትን (ቤተ፡ ክርስቲያን) የመጀመሪያውን ታላቅ መከራና ስደት እናነባለን፤ ከእስጢፋኖስ መገደል በኋላ
(ከሐዋርያት ሥራ ም. 7)፡፡
ምእራፍ ስምንት ስደትና መከራውን (ክርስቶስ ስለ ጽድቅ የተቀበለውን
መከራ መካፈል) ተከትሎ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ የሆነውን መበተን መርዶ በመንገር ይጀምራል፡፡ ይህንን ምእራፍ እንዲህ ከፍለን
ልንረዳው እንችላለን፡ -
1. በክርስትና የመጀመሪያው ታላቅ
መከራ (ከቁ. 1-3)
2. የተበተኑት ምእመናን ወንጌልን
መስበካቸውና ፊልጶስ በሰማርያ (4-8)
3. የሰማርያው ጠንቋይ ሲሞን እና
በዚያ የሆነው (9-24)
4. ወንጌል በሳምራውያን ብዙ መንደሮች
መሰበኩ (ቁ. 25)
5. ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ
(26-40)