Thursday, October 3, 2013

የስንኝ ገበታ 2


        ሐሙስ መስከረም 23/ 2006 የምሕረት ዓመት
 
ሕይወት እንቆቅልሽ ሕይወት አድር ባይ ናት፣
ኢየሱስ በደሙ ጨብጦ ካልያዛት፡፡
ሕሊና ተራቁቶ ማስመሰል ተላብሰን፣
እንዳንክድህ ጌታ ጸጋህ ይጠብቀን፡፡

የሄደ ላይመጣ ላለም ላይቀር መሄድ፣
 ሰው ሰውን ረግጦ አለፈው በመንገድ፣
 ልቤ እጄን ታዘበው ጨብጦ እንዳልሰጠ፣
 አካፍሎ የበላ ሰብስቦ ከራበው እጅጉን በለጠ፡፡

እንዲህ ላለ ኑሮ ማር ሬት ለሚለው፣
የስንቱን ከፍ ዝቅ ዓይኔ አስተዋለው፡፡
ይቸገራል እኔ ወዲያ እየናፈቀ፣
አልገብቶት ለልቤ ሰው እንዳለቀ፡፡

የማይሞቅ የማይበርድ ጣዕም አልባ ኑሮ፣
ወዝውዞ ነዝንዞ መሸ ነጋ ሮሮ፣
የኔ ጌታ ታግኘኝ መምጣትህ፣
ለኔ ረፍት ነውና ያኔ መቃተትህ፡፡ አሜን!

No comments:

Post a Comment