Wednesday, November 18, 2015

የፍቅር ዘመቻዎች


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

                                     እሮብ ህዳር 8 ቀን 2008 የምሕረት ዓመት

1. ሁሉንም ሰው አክብር - ክርስቶስ በሁሉም ሰው ውስጥ ይኖራል፡፡ የሌሎች ሰዎችን ስሜት አክብር - እነርሱ የአንተ ወንድሞችና እኅቶች ናቸውና፡፡

2. ስለ እያንዳንዱ ጥሩ አስብ - በማንም ላይ መጥፎ ነገርን አታስብ፡፡ በመጥፎ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ቢሆን ጥሩ ነገሮችን ለማግኘት ሞክር፡፡

3. ሁልጊዜም ስለ ሌሎች ጥሩ ተናገር - በማንም ላይ ዘለፋን አታድርግ፡፡ በንግግር ካልተገለፀ ቃል የሚመነጨውን ማንኛቸውም ጉዳት አርም፡፡ በሰዎች መካከል ውዝግብና አታካራ እንዲፈጠር ምክንያት አትሁን፡፡

4. ለእያንዳንዱ በፍቅር ቋንቋ ተናገር - ድምጽህን ከፍ አታድርግ፡፡ አትማል፡፡ ሌሎችን አታናድ፡፡ እንባ እንዲፈስ አታድርግ፡፡ ሌሎችን አጽናና፡፡ ደግ ልብ አሳይ፡፡

5. ለእያንዳንዱ ነገር እያንዳንዱን ይቅር በል - ቂም አትያዝ እንደ እርቅ ምልክትነት ሁልጊዜም ቢሆን እርዳታ ለመስጠት የመጀመሪያው ሁን፡፡

6. ሁልጊዜም ቢሆን የግረቤትህን ጥቅም አስቀድም - ለአንተ እንዲደረግልህ እንደምትፈልግ ሁሉ ለሌሎች በጎ ነገርን አድርግ፡፡ ሌሎች ላንተ ሊሰጡህ ስለሚገባቸው እዳ ፈፅሞ አታስብ፣ ነገር ግን ማሰብ የሚኖርብህ አንተ ለሌሎች ስለምትከፍለው እዳ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

7. በችግር ወቅት በንቃት ላይ የተመሰረተ ርኅራኄን አሳይ - ለማጽናናት፣ ለመምከር፣ ለመርዳት፣ ደግ ለመሆን ፍጠን፡፡

8. በንቃት ሥራ - ልክ አንተ ከሌሎች ጉልበት ተጠቃሚ እንደምትሆን ሁሉ ሌሎች ካንተ የሥራ ውጤት ተጠቃሚ ይሆናሉና፡፡

9. ለሕብረተሰብህ ንቁ ሁን - ለድሆችና ለታማሚዎች ደግ ሁን፡፡ ያለህን ሁሉ አካፍል፡፡ በዙሪያህ የሚኖሩት ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ለማየት ሞክር፡፡

10. ጸልይለሁሉም፣ ለጠላቶችህ እንኳን ሳይቀር ጸልይ፡፡
ካርዲናል ስቴፍን ቪሺንስኪ (1900 - 1981)
                                     ‹‹ . . . ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤›› /ቆላ. 4፡3/!


No comments:

Post a Comment