አንተ ጎንበስ እኔ ቀና
የእሾህ አክሊል ደፋህና
የእኔን ላንተ ያንተን ለእኔ
እንዴት ላውራው በምን ቅኔ
ሳትበደር አንተው
ከፋይ
ተመሳቅለህ መስቀሌ
ላይ
ባለ ዕዳው በነፃነት
ተቀመጥኩኝ በሰገነት
መቼ ገብቶኝ ያንተ ነገር
ተጠቅልዬ በሞት ባህር
ፍቅር ፍቅር የሚሆነው
ለካ እንዲሁ ሲወዱ ነው
ያዳም ስዕል ያለህ በዓይኔ
የምሳሳልህ ከብሌኔ
ሁሉን ለአንተ ጠበኩልህ
የልቤን ደጅ ከፈትኩልህ
ተረማመድ በሕይወቴ
ጎጆዬ ነህ ኑሮ ቤቴ
መድኅን ነህ ዋስትናዬ
የሄድኩብህ ቀና ብዬ
በዳይ ባሪያ እኔ ሳለሁ
ለመስቀል ሞት የተገባሁ
ፈራጅ ስትሆን ተፈርዶብህ
የእግዚአብሔር ልጅ ተሰቃየህ
እኔን ሊሸከም ጀርባህ ቆስሏል
ሊፈውሰኝ ደምህ ፈሷል
አንተ ገብተህ በእኔ ስፍራ
አለፈልኝ ያ መከራ
ግጥም፡- በዲ/ን ጋሻዬ /ማሜ/ መላኩ
tsegawn yabzalhe wondeme Gashaye!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteTeremamed behyweta!!
ReplyDeleteGojoyaneh nuro bata!!
Medhn neh wastnaya!!
Yehadkubh kena bya!!
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!