Wednesday, May 8, 2013

የቀርሜሎሱ ጽናት



                                        እሮብ ሚያዝያ 30/2005 የምሕረት ዓመት      

    በዕብራይስጥ ቀርሜሎስ ማለት ፍሬያማ ማለት ሲሆን ኤልያስ በተገለጠ ሁኔታ ብቻውን ከእግዚአብሔር ጋር የቆመበት፣ አምላኩን እንደማያሳፍረው የተወራረደበት ተራራ ነው (1 ነገ. 18)፡፡ ታዲያ በዚህ ተራራ ላይ የኤልያስን ጽናት በግልጥ እንመለከታለን፡፡ በተለይ ከዝሙት ጋር በተያያዘ በአምላኩ ፊት ያሳየውን የእምነት ብርታት እናስተውላለን፡፡ ምክንያቱም እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ጀርባቸውን ሰጥተው ያመልኩት የነበረው በኣል (ጣዖት) አምልኮ ይፈጸምለት የነበረው በዝሙት፣ ራስን በማጎሳቆልና ሰውን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ነበር፡፡ ታዲያ ኤልያስ ለእግዚአብሔር እስራኤል ለጣዖታቸው የአምልኮ ሥነ ስርዓት ለመፈጸምና መሥዋዕት ለማቅረብ ተራራው ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው ኤልያስ እያንዳንዱን ትዕይንት በዓይኑ ተመልክቶአል፡፡


        አምላኬ በሚሉት ጣዖት ፊት ያቀርቡ የነበረውን የዝሙት ሥነ ስርዓት ጭምር (ምን ያህል ፈተና ነበር)፡፡ ዳሩ ግን ኤልያስ በዚህ ውስጥም በእግዚአብሔር አሳብ ጽኑ ነበር፡፡ ዛሬ ሰዎች ስለዚህ ኤልያስ መምጣት መጨነቃቸው ያስገርማል፡፡ ምክንያቱም ያ ለእኛ ከሚኖረው ፋይዳ በላይ የኤልያስን ኑሮ ኖሮ ማለፍ ክብር ስላለው ነው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን በአንድ ነገር ላይ ኑሮ እያነሰ ሲመጣ ምላስ መርዘሙ እሙን ነውና እናንት የምታስተውሉ ሆይ በእሳት ሠረገሎች ወደ ሰማይ ለወጣው ኤልያስ ሳይሆን እንደ ወርቅ በእሳት ለሚፈተነው እምነታችሁ ትጉ!!

1 comment: