Friday, March 2, 2012

ጠባይ ሲመሽ



   ወድዶ አለመዝለቅ፣ የያዙትን አለማጥበቅ፣ ጨበጥ ለቀቅ፣ ኮስተር ሞልቀቅ፣ ከዋሉበት በጎ ጋር አለማንቀላፋት ሰሞነኛው የሰው ጠባይ ነው፡፡ ቀኑን እንደ ዐሥር ሰው ጠባይ ተስተናግደንበት የምንሸኘው፤ ለአንዱ ውኃ ለሌላው እሳት፣ ለአንዱ ማር ለሌላው እሬት፣ ለአንዱ ምንጣፍ ለሌላው እሾህ ጠዋት ትሁት ከሰዓት በኋላ ቁጡ በሆነ ጠባይ ከሁሉም ዓይነት ሆነው የሚያሳልፉ ብዙ ናቸው፡፡

   እንደ ማለዳ ጮራ፣ እንደ ቀትር ፀሐይ ለሁሉም የሚታይና የሚያበራው መልካምነት ከጀንበሯ ጋር አብሮ እየጠለቀ፣ የወዳጅ ጠባይ እየጨለመ፣ ከሁኔታ መክፋት ጋር አብሮ እየከፋ፣ ከሰው ሽሽት ጋር አብሮ እየጠፋ ከልብ ያዘንን ሁሉ ጨለማን የሚገስጽ ብርሃን፣ ሁከት የማይደፍረው ሰላም፣ ሀዘን የማይጋርደው ደስታ፣ ስደት የማያደክመው ዕረፍት፣ ዓመጽ ታግሎ የማይጥለው ብርታት የሁሉም አይን ብቸኛ ተስፋ፣ በየትኛውም ጨለማ ውስጥ መቅረዝ በማንኛውም ብርቱ ሠልፍ መሐል ጽኑ ግንብ ክርስቶስ ኢየሱስ አለላችሁ!

   ሰው ቀን ቢመሽበት ሻማ ለኩሶ ያድራል፡፡ ጠባይ ቢመሽ ግን እንዴት ያንቀላፋል? በተዋበ ሕንፃ ባማረ መንደር በሚስቡ ዕቃዎች ተከብበን ጨለምተኛ አመልን ማስተናገድ አንችልም፡፡ ሰው ጠጉሩን አበጥሮ አለባበሱን አሳምሮ የሕሊናው ጀንበር ካዘቀዘቀች ውጫዊ ምቾት ምን ይረባዋል? የቀንና ሌሊት መፈራረቅ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ የሰው ጠባይ ግን የዝንባሌው ውጤት ነው፡፡ መልካሙን አመል ያዝልቅልን!

      "
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነትህ ብዙ ነው፡፡ ሰቆ.ኤር. 3÷23"

No comments:

Post a Comment