Thursday, December 15, 2011

ጊዜ ይኑርህ


በሕይወትህ ለማቀድ ጊዜ ይኑርህ፤ የብዙ በረከቶች ምንጭ ነውና፡፡
ዓላማህን ከግብ ለማድረስ ጊዜ ይኑርህ፤ የጀመረውን የሚፈጽም ንዑድ ክቡር ነውና፡፡
ተወዳጅ ሆኖ ለመገኘት ጊዜ ይኑርህ፤ የአሳበ ሰፊነት ጎዳናው እርሱ ነውና፡
ቤተሰቦችህን ለማክበር ጊዜ ይኑርህ፤ የረጅም ሕይወት ቃል ኪዳን ነውና፡፡
ለእድሜ ባለጸጎች ጊዜ ይኑርህ፤ ወደ አክብሮት የሚወስደው አውራ ጎዳና ነውና፡፡
ለሕሙማን፣ ለተራቡና ለታሰሩ ጊዜ ይኑርህ፤ ርኅራኄን ማጋራት ነውና፡፡
ለጸሎት ጊዜ ይኑርህ፤ በዓለም ላይ ትልቁ ኃይል እርሱ ነውና፡፡
ለሕይወትህ ጌታ ጊዜ ይኑርህ፤ ብቸኛው ሰላም እርሱ ነውና፡፡
በእርምጃህ ውስጥ ያለውን የሕይወት ቅሬታ መቀበል ከቻልክ፤ ከጥቂት ደስታ ታላቅ የሆነ እርካታ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ትእግሥትና ጥሩ የሆነ አመለካከት ለራስህም ሆነ ለሌሎች ካለህ፤ ፍቅርን መስጠትና የሌሎችንም ፍላጐት መጠበቅ ትችላለህ፡፡ ያለብህን ጉድለት መቀበል ከቻልክ፤ ደስ የሚልና ዘለቄታዊነት ያለው ግላዊ ግንኙነት ይኖርሃል፡፡ ለራስህና ለሌሎች ክብር ከሰጠህ፤ የሰው ዘር አንድ አካል እንደሆንክ ይሰማሃል፡፡ በመንገድህ ከሚመጡ ብዙ ነገሮች ጋር መጣጣም እንደምትችል ከተሰማህ፤ በዙሪያህ ስላሉትና ለልብ ወዳጆህ የኃላፊነት ስሜት ይሰማሃል፡፡

3 comments:

  1. It teachs the value of time. Tebarek ...

    ReplyDelete
  2. በእርምጃህ ውስጥ ያለውን የሕይወት ቅሬታ መቀበል ከቻልክ፤ ከጥቂት ደስታ ታላቅ የሆነ እርካታ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ትእግሥትና ጥሩ የሆነ አመለካከት ለራስህም ሆነ ለሌሎች ካለህ፤ ፍቅርን መስጠትና የሌሎችንም ፍላጐት መጠበቅ ትችላለህ፡፡

    ReplyDelete
  3. Please write write and write.....

    ReplyDelete