Sunday, December 4, 2011

ትኩረት



ለሥራ ትኩረት ስጥ፤ የስኬት ዋጋ ነውና፡፡
ለማስብ ትኩረት ስጥ፤ የኃይል ምንጭ ነውና፡፡
ለደስታ ትኩረት ስጥ፤ በወጣትነት የመቆየት ምስጢር ነውና፡፡
ለማንበብ ትኩረት ስጥ፤ የጥበብ ፏፏቴ ነውና፡፡
ለጸሎት ትኩረት ስጥ፤ ለሕይወት ተገቢን ምላሽ ይሰጥሃልና፡፡
ተግባቢ ለመሆን ትኩረት ስጥ፤ የደስተኝነት መንገድ ነውና፡፡
ለማፍቀርና ለመፈቀር ትኩረት ስጥ፤ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነውና፡፡
ለራዕይ ትኩረት ስጥ፤ የኑሮ ሰረገላህን ወደ ስኬት ያደርስልሃልና፡፡
ዙሪያህን ለመመልከት ትኩረት ስጥ፤ ራስ ወዳድ ለመሆን ቀኑ በጣም አጭር ነውና፡፡
ለማዘንም ሆነ ለመደሰት ትኩረት ስጥ፤ የነፍስ ዜማ ነውና፡፡
ለልግስና ትኩረት ስጥ፤ ሺህ ጊዜ የሚባርክ ደስታ ይፈጥራልና፡
ለእግዚአብሔር ትኩረት ስጥ፤ የሕይወት ብቸኛው የዕድሜ ልክ ወዳጅ እርሱ ነውና፡፡

1 comment: