Friday, December 23, 2011

ከዚህም ጹም


ከቁጣና ከጥላቻ ጹም ለባልንጀሮችህ የበዛ ፍቅርን ስጥ፡፡
ከመለያየት ጹም ቢቻልህስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑር፡፡
በሌሎች ላይ ከመፍረድ ጹም ማንንም ሰው ከመዳኘትህ በፊት እግዚአብሔር ጥፋቶቻችንን እንዴት እንደሚመለከት አስተውል፡፡  
ለራስ ከሚሰጥ አነስተኛ ግምት፣ ከጨለምተኝነትና አሉታዊ ከሆነ አስተሳሰብ ጹም ስለ ሕይወት በሚኖርህ አመለካከት ሁሉ ሚዛናዊ ሁን፡፡  
ተስፋ ከመቁረጥ ጹም ይህ የቁም ሞት ነውና በምታደርገው ነገር ሁሉ ተስፋ ይኑርህ፡፡
ከማጉረምረም ከፍርሃትና ከጭንቀት ጹም ጌታ ለሙሉ ሕይወታችን ያስባልና እምነትህን በእርሱ ላይ ጣል፡፡
ከስንፍና ጹም በሚያስፈልግህ ሁሉ በጸሎትና በምልጃ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቅ፡፡
ሕይወትን ካከበዱብህ ችግሮች፣ ወድቆም ከመቅረት ጹም የደስታዎችህን ጊዜያት ሁሉ ልትደሰትባቸዉ ጣር፡፡
ከምሬት ጹም የደስታዎችህን ጊዜያት ሁሉ ልትደሰትባቸው ጣር፡፡
አብዝቶ ለራስ ከመጨነቅ ጹም ራስህን ምን ጊዜም በጌታ እግር ሥር አድርግ፡፡
ከማንኛውም ዓይነት ቅሬታ አልያም ቂም ጹም የበደሉህን ሁሉ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ይቅር በል፡፡ 
ከአሉባልታና ፌዝ ከተቀላቀለበት ወሬ ጹም እውነተኛ በሆኑና በደስታ ለዛ በተሞሉ ቁም ነገሮች ውስጥ ተሳተፍ፡፡
ከአባካኝነትና ከአጥፊነት ጹም መውጣትና መግባትህ በመጠን ይሁን፡፡ 
ለዓለም አብዝቶ ከመጨነቅ ጹም ተጨማሪ ጊዜ ለአምላክህ ለመስጠት ትጋ፡፡ 
ከክፉ ልማዶችህ ጹም አንተ የተፈጠርከው በእግዚአብሔር አምሳል ነው፡፡
    ልብ በሉ! ዛሬ ምድራችን የምትጨነቀው ከመብል ተከልክለው ነገር ግን ከእነዚህ የክፋት አውራዎች መፆም ባልቻሉ ወገኖች ነው፡፡ ለሚበልጠው ያትጋን!

6 comments:

  1. ከስንፍና ጹም፤ በሚያስፈልግህ ሁሉ በጸሎትና በምልጃ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቅ፡፡
    ሕይወትን ካከበዱብህ ችግሮች፣ ወድቆም ከመቅረት ጹም፤ የደስታዎችህን ጊዜያት ሁሉ ልትደሰትባቸዉ ጣር፡፡

    ReplyDelete
  2. ዛሬ ምድራችን የምትጨነቀው ከመብል ተከልክለው ነገር ግን ከእነዚህ የክፋት አውራዎች መፆም ባልቻሉ ወገኖች ነው፡፡ ለሚበልጠው ያትጋን!

    ReplyDelete
  3. It is real. But we didn't practice ... thank u.

    ReplyDelete
  4. አብዝቶ ለራስ ከመጨነቅ ጹም፤ ራስህን ምን ጊዜም በጌታ እግር ሥር አድርግ፡፡

    ReplyDelete
  5. amen ...tebareku

    ReplyDelete