ለጭንቀት - በጣም ተብረቅራቂ
ለንዴት - በጣም ለጋስ
ለፍርሃት - በጣም ጠንካራ
የመከራን መኖር አምኖ ለመቀበል - በጣም ደስተኛ ሁን፡፡
እውነተኛ ደስታ ከነፍስ፣ ከመንፈስና ከሥጋ ጤንነት ይቀዳል!
በተጨነቅህ ጊዜ፡ -
1. ፈጽሞ ለብቻህ አትጨነቅ፡- ችግሮችህን ለሚያወያይህ ወዳጅ ንገር፡፡ ይህም መንገድ የተጨነቅህበትን ምክንያት በትክክል ለማየት ይረዳሃል፡፡ ከሌሎች መጽናናትንም እንድታገኝ ያደርግሃል፡፡
2. እውነታውን አግኝ፡- የጭንቀትህን መሠረት ፈልግ፡፡ ችግርህን ምክንያት ከሌለው ውጥረትህ እንድትለየው ይረዳሃልና፤ የሚያስጨንቁህም ነገሮች በወረቀት ላይ ለማስፈር ሞክር፡፡
3. ተግባራዊ ሁን፡- ጊዜህን ወይም ደግሞ በመጨነቅ የምታጣውን አቅም አታባክን፡፡ ችግሩ በሚጠይቀው መልኩ ለመፍታት ሞክር፡፡ ቸል ብትል ግን ለወደፊቱ የከፋ ውጥረት ውስጥ ሊከትህ ይችላል፡፡
4. ለጤናህ ከፍተኛ ዋጋ ስጥ፡- ይኽውም ከራስህ፣ ከእግዚአብሔርና ከአካባቢህ ጋር የሚኖርህ ትክክለኛ ግንኙነት ነው፡፡
5. ዛሬን ብቻ ኑር፡- ወደፊት ስለሚሆነው ወይም ደግሞ ባለፈው ስለሆነው ነገር ፈጽሞ አትጨነቅ፡፡ ይልቁንም ደግሞ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ላይ አትጨነቅ፡፡
6. አዎንታዊ አስተሳሰብ ይኑርህ፡- ኑሮ አእምሮ ውስጥ ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን በአሉታዊ አስተሳሰቦች ከመተከዝ ይልቅ በነገሮች መልካም ጎን ላይ አተኩር፡፡ የደስታም ለዛ ይኑርህ፡፡ በትንንሽ ነገሮች መደሰትም ልመድ፡፡
7. ጥቂት ዕረፍ፡- ችግሮችህን የምታጤንበት፣ መፍትሔ ላይ የምትደርሰበት፣ ሁሉን ከሚያውቀው ጌታ ጋር የምትነጋገርበት፣ ጭንቀትህንም የምትሰናበትበት ቢያንስ ግማሽ ሰዓት በእረፍት የማሳለፊያ ጊዜ ይኑርህ፡፡ እየሮጥክ የገጠመህን እየሮጥክ አትፈታውምና፡፡
8. በሥራ ቆይ፡- በመሥራት የምናሳልፈው ጊዜ ከጭንቀት ለመዳን ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ ራስህን በሥራ ላይ ማቆየትህ በአእምሮህ ውስጥ ያሉት አሉታዊ አስተሳሰቦች እንዲጠፋ ያደርጋቸዋል፡፡ እየተማርክ ከሆነም በትምህርትህ ይበልጥ ቀጥል፡፡ ስንፍና የሰይጣን ትልቁ ዙፋን ነውና፡፡
9. ስጦታዎችህን አስብ፡- የበታች እንደሆንክ እየተሰማህ በተጨነክበት ጊዜ ሁሉ የተቸሩህን ስጦታዎች አስብ፡፡ የዚያን ጊዜ የተሻለ ስሜት ይሰማሃል፡፡
በመጨረሻም የሁሉ መጀመሪያ፣ በሂደቱም ላይ ጌታ የሆነውን እግዚአብሔር አስብ፡- በሚያስፈልግህ ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ለእርሱ አሳውቅ፡፡ እርሱ ስለ አንተ ያስባልና በአንዳች አትጨነቅ (ፊልጵ. 4፡6) ።
ከጭንቀትህ የተነሣ በምሽት ለመተኛት ትቸገራለህ፤ ራሳቸውን የሚያሳርፉበት ቀርቶ የሚያስጠጉበት እንኳን የሌላቸውን አስብ፡፡
በሥራህ ደስ የማይል ቀን ያጋጥምሃል፤ ላለፈት ዘመናት ዛሬንም ጨምሮ እንኳን ሥራ አጥቶ የተቀመጠውን ሰው አስብ፡፡
ወዳጅነትህ ወደ ከፋ ጎዳና እያመራ ስለሆነ ተስፋ ቆርጠሃል፤ ማፍቀርና በምላሹ ደግሞ መፈቀር ምን ዓይነት እንደሆነ ጭራሹኑ የማያውቁትን ሰዎች አስብ፡፡
የምትወደውን አንድ ሰው በሞት ስላጣህ ቀኑ ጨልሞብሃል፤ ሙሉ ቤተሰቡን አንድ ቀን የቀበረውን ብቸኝነት እንደ ሳማ ቅጠል የሚለበልበውን እርሱን አስበ፡፡
በሕይወትህ ባጋጠሙህ ጭንቀቶችና በገጠምካቸው ፈተናዎች ትማረራለህ፤ ሁሉም የሆነው ስለኖርክ ነው፡፡ በመቃብር ሥፍራ ካሉት አንዱ እንኳን እንደ አንተ ደስታና ሐዘንን፣ ከፍታና ውድቀትን የማየትም ሆነ የማስተዋል አቅሙም አጋጣሚውም የለውም፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ላለፈው ለሚመጣውና እየሆነ ላለ መጨነቅን አቁም!
እየሮጥክ የገጠመህን እየሮጥክ አትፈታውምና፡፡
ReplyDeleteIt is a good proverb for my life. Thank you!